ስለHUAWEI ክላውድ እና ግላዊነት መግለጫ

HUAWEI ክላውድ መሰረቱን አየርላንድ ውስጥ ባደረገ Aspiegel Limited የሚባል የHuawei ቅርንጫፍ (ከዚህ በኋላ "እኛ" ወይም "የእኛ" በመባል የሚጠራ) የቀረበ አገልግሎት ነው። አንዴ ከገቡ በኋላ ውሂብዎን በማንኛውም መሳሪያ መድረስ እና ማቀናበር እንዲችሉ HUAWEI ክላውድ በራስ-ሰር የእርስዎን ውሂብ ከደመና አገልጋዮች ጋር ያቀናጃል፣ ምትኬ ያስቀምጣል እና ይሰቅላል።

ይህ መግለጫ የሚከተሉትን ይገልጻል፦

1. ስለእርስዎ የምንሰበስበው ውሂብ ምንድን ነው?

2. የእርስዎን ውሂብ የምንጠቀምበት እንዴት ነው?

3. ውሂብዎን የምናስቀምጠው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

4. የእርስዎን ውሂብ የምናጋራው እንዴት ነው?

5. የእርስዎ መብቶች እና አማራጮች ምንድን ናቸው?

6. እኛን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል?

7. ይህን መግለጫ እንዴት ነው የምናዘምነው?

1 ስለእርስዎ የምንሰበስበው ውሂብ ምንድን ነው?

እንደ የHUAWEI ክላውድ አገልግሎት አካል የግል ውሂብዎን የምንሰበስበውና የምንጠቀምበት በዚህ መግለጫ ውስጥ ለተጠቀሱት ዓላማዎች ብቻ ነው። የግል ውሂብ ማለት እኛ እርስዎን እንደ አንድ ተጠቃሚ ለይተን እንድናውቀዎት የሚያስችለን ማንኛውም መረጃ ማለት ነው።
የሚከተለውን ውሂብ ሰብስበን እናሰናዳለን፦

የመለያ መረጃ፦ እንደ የመለያ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ የመገለጫ ስዕል፣ የተጠቃሚ ስም፣ የሀገር ኮድ፣ የመለያ ለዪ እና የተጠቃሚ አገልግሎት ቶከን ያለ።

የመሳሪያ መረጃ፦ እንደ የመሳሪያ መታወቂያ (በሰርዓተ ክወናዎ የሚወሰን ሆኖ እንደ MEID፣ UDID ወይም IMEI ያለ)፣ OAID፣ የመሳሪያ ሞዴል፣ ስርዓተ ክወና የኤፒኬ ስሪት እና የቋንቋ ቅንብሮች ያለ።

የአውታረ መረብ መረጃ፦ እንደ የIP አድራሻ፣ አውታረ መረብ አይነት እና የግንኙነት ሁኔታ ያለ።

የአገልግሎት አጠቃቀም መረጃ፦ እንደ የHUAWEI ክላውድ ስሪት፣ የወረደበት ምንጭ፣ መተግበሪያ የተከፈተበት እና የተዘጋበት ሰዓት፣ የተጫኑ መተግበሪያዎች ዝርዝር፣ ጠቅታዎች እና ተጋላጭነት፣ የጥቅል መረጃ (ስም፣ አቅም እና የቆይታ ጊዜ)፣ የግዢ መረጃ (ጊዜ፣ መጠን እና የትዕዛዝ መታወቂያ)፣ የስርዓት መዝገቦች እና የስህተት መዝገቦች ያለ።

የተቀናጀ፣ ምትኬ የተቀመጠለት ወይም የተሰቀለ ውሂብ (በተመዘገበው የእርስዎ HUAWEI መታወቂያ ሀገር/ክልል ውስጥ እንዳሉት ባህሪዎች ውጤቶች ሊለያዩ ይችላሉ)፦ እንደ የተቀናጀ ውሂብ (እውቂያዎች፣ የቀን መቁጠሪያ ክስተቶች፣ የWi-Fi ቅንብሮች፣ ማስታወሻዎች፣ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ጨምሮ)፣ የክላውድ ምትኬ ውሂብ (እውቂያዎች፣ የቀን መቁጠሪያ ክስተቶች፣ የWi-Fi ቅንብሮች፣ ማስታወሻዎች፣ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች፣ ቅጂዎች፣ የጥሪ መዝገብ፣ የትንኮሳ ማጣሪያ እና ቅንብሮች፣ መልዕክቶች፣ የስልክ አስተዳደር ቅንብሮች፣ የአሳሽ እልባቶች፣ የአየር ሁኔታ ቅንብሮች፣ የማያ አቀማመጥ፣ የካሜራ ቅንብሮች፣ የስልክ ቅንብሮች፣ የኤፍኤም ሬዲዮ ቅንብሮች፣ የማንቂያ ቅንብሮች፣ የSmartCare ቅንብሮች እና የተጫኑ መተግበሪያዎች ዝርዝር ጨምሮ)፣ የHuawei አንጻፊ ፋይሎች (ለመስቀል የመረጧቸው ማናቸውም አካባቢያዊ ፋይሎችም ጨምሮ) እና የባንክ ካርዶችዎን በክላውድ ድር ጣቢያ ላይ ለማስተዳደር (ለማስወገድና ለማገድ) የሐሰት ስም የባንክ ካርድ ቁጥር (የመጨረሻዎቹ አራት አኃዞች)። የባንክ ካርዱ መረጃ በክላውድ ላይ አይከማችም።


ውሂብዎን ለማቀናበር በእርስዎ የHUAWEI መታወቂያ ወደ ኦፊሴላዊው የHUAWEI ክላውድ ድር ጣቢያ (cloud.huawei.com) ከገቡ የሚከተለው መረጃም እንዲሁም ይሰበሰባል፦

አሳሽ እና ተጠቃሚ መረጃ፦ እንደ ኩኪዎች፣ የIP አድራሻ፣ የአሳሽ ዓይነት፣ የሰዓት ክልል፣ ቋንቋ እና የመዳፊት እና የቁልፍ ሰሌዳ ክወና። በኩኪስ ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የእኛን የኩኪ ፖሊሲ ያንብቡ።

HUAWEI ክላውድ የማቀናጀት እና ምትኬ የማስቀመጥ አገልግሎትን ማቅረብ እንዲችል የመሳሪያ መረጃ ለማግኘት ስልኩን የመድረስ እና የማከማቻ፣ የካሜራ፣ የመልእክት መላኪያና መቀበያ፣ እውቂያዎች እና የቀን መቁጠሪያ ፈቃዶች ያስፈልጉታል።

2 የእርስዎን ውሂብ የምንጠቀምበት እንዴት ነው?

ክላውድ ቅንጅት፣ ክላውድ ምትኬ፣ Huawei አንጻፊ እና ሌሎች የውሂብ አገልግሎቶችን ጨምሮ ወሳኝ የHUAWEI ክላውድ ተግባራትን ለመተግበርና እንዲሁም የውል ግዴታዎችን ለመወጣት መተግበሪያው የእርስዎን ውሂብ ለደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር፣ ለድጋፍ እና ተግባቦት፣ ለደንበኛ ቅሬታ አያያዝ፣ ጥገና፣ የሶፍትዌር እና የስርዓት ዝማኔ፣ የተጠቃሚ መለያ እና ለምርመራና ጥገና ዓላማዎች መሰብሰብ እና ማሰናዳት አለበት።

በተጨማሪም፣ በህጋዊ ፍላጎቶች መሰረት የእርስዎን የግል ውሂብ ለሚከተሉት አላማዎች እንጠቀምበታለን፦

የስታትስቲክስ እና የምርት ማሻሻያ አላማዎች፣ በእርስዎ የአጠቃቀም እንቅስቃሴ ላይ በመመስረት የተጠቃለሉ ቡድኖችን መፍጠር ጨምሮ። ይህ የተጠቃሚዎቻችንን ፍላጎቶች እንድንረዳ እና የአሁን እና የወደፊት አገልግሎቶቻችን እና አቅርቦታችን ጥራት እና የተጠቃሚ ተሞክሮ እንድናሻሽል ያስችለናል። ከታች በአንቀጽ 5.5 ላይ እንደተገለጸው እንደዚህ ያለውን ማሰናዳት መቃወም ይችላሉ።

የእኛን አቅርቦት፣ የሽያጭ ማስተዋወቂያ እና ሌሎች የገበያ ዓላማዎች ጨምሮ የገበያ ስራ ዓላማዎችና እንዲሁም ለገበያ ስራ የተጠቃለሉ የታለሙ ቡድኖችን ስለመፍጠር መረጃ መስጠት። የደንበኛዎቻችን ምርጫዎች ማወቅ አቅርቦታችንን እንድናነጣጥር እና ደንበኛዎቻችን ፍላጎቶችና የሚጠብቁትን ነገር በተሻለ የሚያሟሉ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን እንድናቀርብ ያስችለናል። ከታች በአንቀጽ 5.5 ላይ እንደተገለጸው እንደዚህ ያለውን ማሰናዳት መቃወም ይችላሉ።

የመረጃ ደህንነት ዓላማዎች፣ ደህንነታቸው የተጠበቁ እና አስተማማኝ አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ የተለያዩ ዓይነት የአገልግሎቶች ያለአግባብ አጠቃቀሞችን እና ማታለሎችን መግለጽ ወይም መከላከል ጨምሮ።

ሲያስፈልግ ከአገልግሎት ጋር የሚገናኙ ማሳወቂያዎችን (እንደ የስርዓት ጥገና ማስታወቂያዎች፣ የግብይት መዛግብት እና የደመና ማከማቻ አጠቃቀም አስታዋሾች ያሉ) ልንክልዎ እንችላለን። በባህሪያቸው የማስተዋወቂያ ያልሆኑ ከአገልግሎት ጋር የሚዛመዱ አስፈላጊ ማሳወቂያዎችን ከመቀበል መርጠው መውጣት ላይችሉ ይችላሉ።

እንዲሁም እኛን በሚመለከታቸው ህጎች እና ደንቦች መሠረት የእርስዎን ጥቅል እና የግዢ መረጃ ለግብር እና ለሒሳብ ስራ ዓላማዎች ልናሰናዳ እንችላለን።

3 ውሂብዎን የምናስቀምጠው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

የእርስዎን የግል ውሂብ የምናስቀምጠው በዚህ መግለጫ ውስጥ ለተጠቀሱት ዓላማዎች አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው።

የእርስዎ ውሂብ የደንበኛ ግንኙነቱ እስከሚቆይበት ጊዜ ድረስ እናሰናዳለን እና እናስቀምጣለን። HUAWEI ክላውድን ለአስራ ሁለት (12) ወራት መጠቀም ካቆሙ ውሂብዎ ይሰረዛል። በዚህ ሁኔታ ላይ ስለስረዛው አስቀድመን በኢሜይል እና በሌሎች አግባብ በሆኑ መንገዶች እናስታውሰዎታለን። የእርስዎን የHUAWEI መታወቂያ ሲሰርዙ ከእርስዎ መለያ ጋር የሚዛመድ የግል ውሂብ እና እንደ HUAWEI ክላውድ ያሉ ተጓዳኝ አገልግሎቶቹ ይደመሰሳሉ። ይሁንና የሚከተሉትን እናቆያለን፦

የHUAWEI ክላውድ ጥቅል እና የግዢ መረጃ ግብይቱ ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ ለሰባት (7) ዓመታት።

ለደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር ዓላማ የተሰናዳ የግል ውሂብ (እንደ ቅሬታዎች፣ የውሂብ ጉዳይ ጥያቄዎች እና የውል አስተዳደር መረጃ ያለ) የHUAWEI መታወቂያ ከተሰረዘ በኋላ እስከ አምስት (5) ዓመታት፤ ለትንታኔያዊ ትንተና እና ምርት ግንባታና እንዲሁም ለሽያጭ ማስተዋወቅ እና የገበያ ዓላማዎች ጥቅም ላይ የሚውል ውሂብ ከተሰበሰበበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አስራ ሁለት (12) ወራት፣ እንዲህ ያለ መሰናዳት ካልተቃወሙ በስተቀር።

የእርስዎ ውሂብ እና አገልግሎቶች ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሰናዱ የውሂብ ምትኬዎች እና የመተግበሪያ መዝገቦች፣ ከተፈጠሩበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት (6) ወራት።

የእንቅስቃሴ እና የስርዓት መዝገቦች የሚመለከተው ስታቲስቲካዊ ትንተና ሲጠናቀቅ ወዲያውኑ ይሰረዛሉ፤ የስህተት መዝገቦች ከተሰበሰበበት ዕለት ከሰባት (7) ቀናት በኋላ በራስ-ሰር ይሰረዛሉ።

የማቆያ ጊዜው ሲያበቃ በሚመለከታቸው ህጎችና ደንቦች እስካልተጠየቀ ድረስ የግል ውሂብዎን እንሰርዛለን ወይም ማንነት እንዳይገልጽ እናደርገዋለን።

4 የእርስዎን ውሂብ የምናጋራው እንዴት ነው?

ውሂብዎን የምናከማቸው በሩሲያ ውስጥ በሚገኙ የውሂብ ማዕከላት ላይ ነው። ከሩሲያ ፌዴሬሽን እንደ አየርላንድ እና ፊንላንድ ያሉ ከአህ/ኢኢኤ እና ሩሲያ ፌዴሬሽን ውጭ ወዳሉ ሌሎች አገሮች ድንበር-ተሻጋሪ የግል ውሂብ ማስተላለፍ ልናካሄድ እንችላለን። እርስዎ እንግዲህ በሩሲያ ፌዴሬሽን ህግ መሠረት የግል ውሂብዎን ከሩሲያ ፌዴሬሽን ውጭ ወደሚገኙ አገሮች ለማስተላለፍ የሚያስፈልገውን ፈቃድ ሰጥተውናል።

የእርስዎን ውሂብ የምናጋራው በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ ብቻ ነው፦

በሚመለከታቸው ህጎች መሠረት ወይም ከህጋዊ ሂደት ጋር በተያያዘ ለህጋዊ ሂደት ወይም ስልጣን ካለው አካል ለመጣ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሲያስፈልግ።

እንደ የውህደት፣ የግዢ፣ የእሴቶች (እንደ የአገልግሎት ስምምነቶች ያሉ) ሽያጭ ወይም የአገልግሎት ወደ አንድ የHuawei ቡድን ህጋዊ አካል ወይም ሌላ ኩባንያ ሽግግር አንድ አካል ሲያስፈልግ።

5 የእርስዎ መብቶች እና አማራጮች ምንድን ናቸው?

የሚከተሉት መብቶች እና አማራጮች አለዎት፦

5.1 የእርስዎን ውሂብ መድረስ

በመሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች (Settings) > የHUAWEI መታወቂያ (HUAWEI ID) > የግላዊነት ማእከል (Privacy center) > የእርስዎን ውሂብ ይጠይቁ (Request your data) በመሄድ የሰብሰብነው እና በHUAWEI ክላውድ ውስጥ ያከማቸነው የግል ውሂብዎ ቅጂ እና ገላጭ መጠየቅ ይችላሉ።

እንዲሁም እርስዎ ያቀናጁትን፣ ምትኬ ያስቀመጡለትን ወይም የሰቀሉትን ውሂብ ከHUAWEI ክላውድ መተግበሪያ ወይም ኦፊሴላዊ ድር ጣቢያ (cloud.huawei.com) መድረስ ወይም ማውረድ ይችላሉ።

ለተጨማሪ የመዳረሻ ጥያቄ እባክዎ ያነጋግሩን

5.2 የእርስዎን ውሂብ ማስተካከል

ውሂብዎን ወቅታዊ እና ትክክለኛ እንደሆነ ለማቆየት በመሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች (Settings) > የHUAWEI መታወቂያ (HUAWEI ID) በመሄድ ውሂብዎን መድረስ እና መቀየር ይችላሉ።
እርስዎ ያቀናጁትን፣ ምትኬ ያስቀመጡለትን ወይም የሰቀሉትን ውሂብ ከHUAWEI ክላውድ መተግበሪያ ወይም ኦፊሴላዊ ድር ጣቢያ (cloud.huawei.com) መድረስ እና መቀየር ይችላሉ።

5.3 የእርስዎን ውሂብ ማዛወር

በመሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች (Settings) > የHUAWEI መታወቂያ (HUAWEI ID) > የግላዊነት ማእከል (Privacy center) > ውሂብዎን ይጠይቁ (Request your data) በመሄድ በHUAWEI ክላውድ ላይ ለእኛ ያቀረቡት የግል ውሂብ በተለምዶ ስራ ላይ በሚውል እና ሊነበብ ወደሚችል ቅርጸት ማዛወር ይችላሉ።
እንዲሁም እርስዎ ያቀናጁትን፣ ምትኬ ያስቀመጡለትን ወይም የሰቀሉትን ውሂብ ከHUAWEI ክላውድ መተግበሪያ ወይም ከኦፊሴላዊው ድር ጣቢያ (cloud.huawei.com) ማውረድ ይችላሉ።

5.4 የእርስዎን ውሂብ መደምሰስ

እርስዎ በማንኛውም ጊዜ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦

የእርስዎን የተቀናጁ፣ ምትኬ የተቀመጠላቸው እና ሌሎች የመተግበሪያ ውሂብ ዓይነቶች ከመሳሪያዎ ላይ በመሰረዝ ማጥፋት ይችላሉ። ስረዛው በራስ-ሰር ከደመናው ጋር ይቀናጅና ያዘምነዋል።

በቀጥታ በHuawei አንጻፊ ላይ በመሰረዝ የተከማቸውን ውሂብዎ ይሰርዙ።

እውቂያዎች፣ ፎቶዎች፣ ቅጂዎች፣ የእግድ ዝርዝር እና የHuawei አንጻፊ ፋይሎች ጨምሮ የእርስዎን ውሂብ ለመሰረዝ ወደ ኦፊሴላዊው የHUAWEI ክላውድ ድር ጣቢያ (cloud.huawei.com) ይግቡ።

የእርስዎን HUAWEI መታወቂያ መሰረዝ። ይህ በHUAWEI ክላውድ ውስጥ ያለውን የግል ውሂብዎን ጨምሮ ከእርስዎ የHUAWEI መታወቂያ ጋር የተጎዳኘ የግል ውሂብዎን ይደመስሳል።

አንቀጽ 5.5 ውስጥ በተገለጸው መሠረት የግል ውሂብዎ መሰናዳትን መቃወም። ተቃውሞዎ ትክክለኛ ከሆነ እና ውሂብዎን ማሰናዳቱን ለመቀጠል ሕጋዊ መሰረት የሌለን ከሆነ በእርስዎ ሕጋዊ ተቃውሞ ወሰን ውስጥ የሚወድቀውን ውሂብ እንደመስሳለን።

የግል ውሂብዎ መሰናዳት ህገወጥ እንደሆነ እና ውሂብዎ መደምሰስ እንዳለበት ካሰቡ ያነጋግሩን

5.5 መሰናዳትን መቃወም

የእርስዎ ውሂብ ለስታቲስቲካዊ፣ ለምርት ማሻሻል ወይም ለሽያጭ እና ለገበያ ዓላማዎች መሰናዳቱን የሚቃወሙ ከሆነ እባክዎ ያነጋግሩን

ጥያቄውን ሲያቀርቡ እባክዎ የጥያቄውን ወሰን ይግለጹና በእርስዎ የHUAWEI መታወቂያ ወደ HUAWEI ክላውድ ለመግባት የሚጠቀሙበትን የእርስዎን ኢሜይል አድራሻ ወይም የስልክ ቁጥር ይስጡን።

ባቀረቡት ጥያቄ ለመቀጠል የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ እናነጋግረዎታለን።

5.6 ማሰናዳትን መገደብ

የእርስዎን የግል ውሂብ መሰናዳትን መገደብ ከፈለጉ እባክዎ ያነጋግሩን። በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ የውሂብዎ መሰናዳት የመገደብ መብት አለዎት፦

ውሂብዎ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ተሰናድቷል፣ ነገር ግን መደምሰስ አይፈልጉም።

ሊመሰርቱት፣ ሊጠቀሙት ወይም ሊከላከሉት የሚያስፈልገዎት እና ውሂብዎን ሳንጠብቅ ስንቀር እንድንጠብቀው ሊጠይቁን የሚችሉት ህጋዊ የይገባኛል ጥያቄ አለዎት።

የተቃውሞ ጥያቄዎ የእኛን ማረጋገጥ በመጠባበቅ ላይ ነው።

ጥያቄዎን ሲያስገቡ እባክዎን የጥያቄውን ወሰን እና መሰረት ይግለጹና ወደ የእርስዎን HUAWEI ክላውድ ለመግባት የሚጠቀሙበትን የእርስዎ ኢሜይል አድራሻ ወይም የስልክ ቁጥር ይስጡን።

ባቀረቡት ጥያቄ ለመቀጠል የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ እናነጋግረዎታለን።

6 እኛን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል?

አንቀጽ 5 ውስጥ የውሂብ ጉዳይ መብቶችዎን እንዴት እንደሚጠቀሙ ምክር ማግኘት ይችላሉ። እንደ የውሂብ ባለጉዳይ በእርስዎ መብቶች ላይ ወይም የግል ውሂብዎ በHuawei መሰናዳትን በተመለከት ማናቸውም ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች ወይም ጥቆማዎች ካለዎት፣ ወይም ደግሞ የውሂብ ጥበቃ ኃላፊያችንን ማነጋገር ከፈለጉ እባክዎ ያነጋግሩን

የዋና መስሪያ ቤታችን አድራሻ፦ Aspiegel Limited, 1F, Simmonscourt House, Ballsbridge, Dublin 4, D04 W9H6, Ireland። የምዝገባ ቁጥር 561134።

እኛ የግል ውሂብዎን በመግለጫው ወይም በሚመለከታቸው የውሂብ ሕጎች መሰረት አላሰናዳንም ብለው የሚያምኑ ከሆነ በአካባቢዎ የሚገኘው የውሂብ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር ወይም በአየርላንድ ውስጥ የውሂብ ጥበቃ ኮሚሽነር ጋር ቅሬታዎን ማቅረብ ይችላሉ።

7 ይህን መግለጫ እንዴት ነው የምናዘምነው?

በጊዜ ሂደት ልናዘምነው ስለምንችል የዚህ መግለጫ የቅርብ ጊዜውን ስሪት በመተግበሪያ ቅንብሮች ላይ በመደበኝነት እንዲመለከቱት እናበረታታዎታለን። በዚህ መግለጫ ላይ የይዘት ለውጦች የተደረጉ እንደሆነ በለውጡ ባህሪ የሚወሰን ሆኖ በማሳወቂያ መገናኛዎች፣ ተገፊ መልዕክቶች፣ ኢሜይሎች እና በመሳሰሉት እናሳውቀዎታለን።

መጨረሻ የተዘመነው፦ ጁላይ 3 ቀን፣ 2019 ዓ.ም